Scroll to top
Address
People to People
P.O. Box 1209
54983 Lexington, KY 40555
General inquiry:
info@jegnaworks.org

የኮቪድ-19 ዘመቻ

ኮቪድ-19ን እንዋጋ

የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመዋጋት ጀግና እና ፒፕል ቱ ፒፕል ከከፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና አርትስ ቲቪ ጋር በመተባበር የህዝብ ግንዛቤ ዘመቻ ጀምረዋል:: ዘመቻው ጠቃሚ የጤና ባለሙያዎችን ምክር በዚህ የፌስቡክ ድረ ገጽ ላይ በጥያቄና መልስ መልክ በማቅረብ ላይ ይገኛል:: እርስዎም ይህንን ድረ ገጽ እንዲቀላቀሉ እንጋብዝዎታለን::

የዘመቻው አላማ

We Talk

የእትዮጵያን ሕዝብ ስለኮቪድ ማስተማርና ጥንቃቄ እንዲወስዱ ማበረታት

ጫና መቀነስ

በፌደራል ጤና ጥበቃ የስልክ ጥሪ ማዕከላት ላይ ያለውን ጫና መቀነስ

የተሳሳተ መረጃን መዋጋት

ሕዝቡን ከጤና ባለሙያዎች ጋር በማገናኘት ትክክለኛና የማያሻማ መረጃ መስጠት የተሳሳተ መረጃን መዋጋት

የሚዲያ ይዘቶች

እነዚህን ጠቃሚ መረጃዎች በተለያዩ የማሕበራዊ ድረ ገጶችና የመገናኛ አውታሮች ላይ በመጋራት ኮቪድ-19ን እንዋጋ::

ጥያቄና መልስ

እነዚህን ጠቃሚ መረጃዎች በተለያዩ የማሕበራዊ ድረ ገጶችና የመገናኛ አውታሮች ላይ በመጋራት ኮቪድ-19ን እንዋጋ::

ስለጤና ባለሙያዎቹ

የሕዝቡን ጥያቄ በመመለስ ግንዛቤ ስለሚያስጨብጡት የጤና ባለሙያዎች በዚህ ድረ ገጽ ላይ ማንበብ ይችላሉ::

ስለኮቪድ-19 መሰረታዊ ጥያቄዎች

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

ኮሮና ቫይረስ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ በሽታን የሚያስከትል ስፋት ያለው የቫይረስ ዝርያ ነው። ከጉንፋን እስከ አደገኛ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች ለሆኑት መርስ እና ሳርስ የሚዳርጉ የተለያዩ ኮሮና ቫይረሶች አሉ። በቅርቡ የተገኘው ኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 የተባለውን የኮሮና በሽታ የሚያስከትል ነው።

ኮቪድ-19 ምንድነው?

ኮቪድ-19 በቅርቡ በተገኘው ኮሮና ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። ይህ አዲሱ በሽታም ሆነ ቫይረሱ በታህሳስ 2019 በውሀን ቻይና ግዛት ከተከሰተው ወረርሽኝ በፊት አይታወቅም ነበር።

በጠና የመታመም ተጋላጭነት ያለው ማነው?

በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ እና የተለያዩ በሽታዎች( እንደ ደም ግፊት፣ የልብ በሽታ፣ ካንሰር ወይም የስኳር በሽታ እና የመሳሰሉት) ያሉባቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ይበልጥ በጠና የመታመም አደጋ ያጋጥማቸዋል፡ ሌሎች ተጨማሪ ጥናቶች በዚህ ዙሪያ እየተሰሩ ይገኛሉ።

አንቲባዮቲክስ ኮቪድ-19ን ለመከላከል ወይም ለማከም ይረዳል?

አንቲባዮቲክስ ቫይረስን ለማከም አይረዳም፤ አንቲባዮቲክስን በባክቴሪያ አማካኝነት ለሚመጣ በሽታ ብቻ  የምንጠቀምበት ነው፤ ኮቪድ-19 የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ስለሆነ አንቲባዮቲክስ ኮቪድ-19ን ለማከምም ሆነ ለመከላከል አያገለግሉም ፤ አንቲባዮቲክስን ሀኪሞች እንደሚያዙት በባክቴሪያ ለሚመጣ በሽታ ብቻ መጠቀም አለብን።

🥄 ቫይረሱ ባረፈባቸው እቃዎች ላይ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?

ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በተለያየ እቃዎች ላይ የተለያየ ጊዜ ይቆያል፣

 • በፕላስቲክ ላይ 5 ቀን፣
 • በእንጨት ላይ 4ቀን፣
 • በብርጭቆ ላይ 4 ቀን፣
 • በወረቀት ወይም በካርቶን ላይ 1 ቀን፣
 • በእጅ ጓንት ላይ ከ 4-5 ቀን፣
 • በብረት ላይ 2 ቀን ይቆያል። በሌሎች እቃዎች ላይ የሚቆይበት ጊዜ ገና እየተጠና ይገኛል።
 • የእቃዎች ገጵ ተበክለዋል ብለው ካሰቡ እራስዎን እና ሌሎችን ከቫይረሱ ለመከላከል ቀለል ያሉ ጰረ-ብክለት ኬሚካሎችን (እንደ በረኪናና አልኮል ወይም በሳሙናና በዉሃ) ተጠቅመው በሚገባ ያጵዿቸው፤ እጅዎን ከአልኮል በተሰሩ ጰረ-ብክለት ኬሚካሎች ወይም በሳሙና እና በውሀ ይታጠቡ፤ አይንዎን አፍንጫዎን እና እፍዎን ከመነካካት ይቆጠቡ።

የኮቪድ-19 የመራቢያ ጊዜ ምን ያህል ነው?

“የመራቢያጊዜ” ማለት ቫይረሱ ሰውነታችን ውስጥ ገብቶ ምልክቶችን ማሳየት እስኪጀምር ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፤ የኮቪድ-19 የመራቢያ ጊዜ ከ1-14 ቀን እንደሆነ ይገመታል፤ ይሄ ግምት ተጨማሪ መረጃዎች ሲገኙ ሊቀየር ይችላል

ኮቪድ-19 ማለት ሳርስ ማለት ነው?

አይደለም፤ ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ እና በ2003 እኤአ ከባድ እና ድንገተኛ የመተንፈሻ አካልን በሽታ ያስከተለው(SARS)  ቫይረስ ዝርያችው  አንድ ቢሆንም የሚያስከትሉት በሽታ ግን ፈጽሞ የተለያየ ነው

SARS ከኮቪድ-19 ይበልጥ ገዳይ እንደሆነ ይታወቃል፤ ከ2003 በኋላ የሳርስ ወረርሽኝ በየትኛውም ሀገር አልተከሰተም

የኮቪድ-19 ምልክቶች ምን ምን ናቸው?

በአብዛኛው ጊዜ የሚታዩ የኮቪድ-19 ምልክቶች፡

 • 🤒 ትኩሳት
 • 😴 ድካም
 • 💨 ሳል

አንዳንድ በሽተኞች ህመም ሊሰማቸው ይችላል፤ የአፍንጫ መደፈን ወይም ፈሳሽ መብዛት የጉሮሮ ህመም እና ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል

በአብዛኛው እነዚህ ምልክቶች መለስተኛ እና ቀስ በቀስ መታየት የሚጀምሩ ናቸው፤ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ቢያዙም እነዚህ ምልክቶችም ሆኑ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል

መድሃኒቶች / ክትባቶች

ኮቪድ-19ን ለመከላከል ወይም ለማዳን የሚጠቅሙ መድሀኒቶች አሉ?

አንዳንድ ምእራባዊ፣ ባህላዊ እና በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ መድሀኒቶች የኮቪድ-19 በሽታን ምልክቶች ቀለል ለማድረግ ሊያግዙ ቢችሉም፤ እነዚህ መድሀኒቶች በሽታውን ለመከላከልም ሆነ ለማዳን እንደሚረዱ የተረጋገጠ ነገር የለም፤ የዓለም የጤና ድርጅት አንቲባዮቲክስም ሆነ እነዚህን መድሀኒቶች ተጠቅመን ራሳችንን ከበሽታው እንድንከላከል ወይም እንድናክም አይረዱንም፤ ሆኖም ምእራባዊው እና ባህላዊው ህክምና ላይ የተለያዩ ጥናቶች እየተደረገ ነው፤ የዓለም የጤና ድርጅት አዳዲስ  የህክምና ግኝቶችን በተቻለ ፍጥነት ለህዝብ ይፋ ማድረጉን ይቀጥላል።

ኮቪድ-19 ክትባት፤ መድሀኒት ወይም ህክምና አለው?

እስካሁን ድረስ ኮቪድ-2019 ክትባትም ሆነ ከቫይረሱ የሚያድን መድሀኒት አልተገኘለትም፤ ሆኖም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የበሽታው ምልክቶች ቀለል እንዲልላቸው ህክምና ሊያገኙ ይገባል፤ በጠና የታመሙ ሰዎች ሆስፒታል መተኛት አለባቸው፤ በሚደረግላቸው ድጋፋዊ ህክምና ብዙዎች ይድናሉ

ክትባቶች እና አንዳንድ መድሀኒቶች በላብራቶሪ ሙከራዎች እየተጠኑ ናቸው፤ የዓለም ጤና ድርጅት COVID-19 ን ለመከላከል እና ለማከም ክትባቶችን እና መድሃኒቶችን ለመስራት ጥረቶችን እያስተባበረ ነው።

እራስዎን እና ሌሎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል የሚረዱ ዘዴዎች፡ በተደጋጋሚ እጅን መተጠብ በሚያስሉበት ጊዜ አፍዎን እና አፍንጫዎን በክንድዎ መሸፈን እና ከሚያስሉ ሰዎች ቢያንስ 2 ሜትር (2 የአዋቂ እርምጃ) እርቀት መጠበቅ

መተላለፊያ መንገዶች

የኮቪድ-19 በሽታ ምልክት ያልታየበት ሰው በሽታውን ሊያስተላልፍ ይችላል?

በሽታው በዋነኝነት የሚተላለፈው በበሽታው ከተያዘ ሰው የመተንፈሻ አካል በሚወጣ እርጥብት አዘል ብናኞች ነው፤ ምንም አይነት ስሜት ያልታየበት ሰው በሽታውን የማስተላለፍ እድሉ በጣም አናሳ ነው፤ ነገር ግን በኮቪድ-19 የተያዙ ብዙ ሰዎች መጠነኛ የሆነ ምልክቶችን ነው የሚያሳዩት፤ በተለይም ደግሞ ወደመጀመርያ አካባቢ። ለምሳሌ ያህል መጠነኛ ሳል ካለው ነገር ግን የህመም ስሜት ከማይሰማው ሰው ኮቪድ-19 ሊይዘን ይችላል።

ሰዎች በእንስሳት አማካኝነት በኮቪድ-19 ሊያዙ ይችላሉ?

ኮሮና ቫይረስ በእንስሳቶች ላይ ከተለመዱ ቫይረሶች መሀከል አንዱ ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በነዚህ ቫይረሶች ይያዛሉ፤ ወደሌሎች ሰዎችም ያስተላልፋሉ፤ ለምሳሌ SARS-CoV ከድመቶች ጋር ቁርኝት ነበረው፤ MERS-CoV ደግሞ ከግመሎች ጋር ቁርኝት ነበረው፤ እስካሁን ድረስ ግን ኮቪድ-19 ከእንስሳት ጋር ቁርኝት ይኑረው አይኑረው የተረጋገጠ መረጃ የለም። ነገር ግን ከእንስሳት እና ከእንስሳት ጋር ንክኪ ካለው እቃም ሆነ ወለል ጋር ከተነካኩ እጅዎን በሳሙናና በውሃ ይታጠቡ፤ ባልበሰሉ ምግቦች አማካኝነት የሚመጣን መመረዝ ለመከላከል ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋእጾዖ ከመመገብ ይቆጠቡ።

ኮቪድ-19 ከቤት እንስሳ ወደ ሰው ሊተላለፍ ይችላል?

ውሻ ድመት ወይም የተለያዩ የቤት እንስሳት ኮቪድ-19ን ሊያስተላልፉ እንደሚችል የተረጋገጠ መረጃ የለም፤  ኮቪድ-19 በዋነኝነት የሚሰራጨው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ሲያስሉ ሲያስነጥሱ ወይንም ሲያወሩ ከመተንፈሻ አካላቸው በሚወጡ እርጥብት አዘል ብናኞች አማካኝነት ነው፤ እራስዎን ለመከላከል የበሽታውን መከላከያ መንገዶች ይተግብሩ።

ኮቪድ-19 በሽታው ካለበት ሰው ዐይነምድር ሊይዘኝ ይችላል?

በበሽታው በተያዘ ሰው ዐይነምድር አማካኝነት በኮቪድ-19 የመያዝ እድል ዝቅተኛ ነው፤ ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች ቫይረሱ በዐይነምድር ውስጥ ሊገኝ እንደሚችል ቢጠቁሙም፤ በዚህ መንገድ መሰራጨት ግን የወረርሽኙ ዋነኛ መገለጫ አይደለም፤ የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19ን ስርጭት በተመለከተ ቀጣይ ጥናቶችን እያካሄደ ነው፤ ተጋላጭነትን ስለሚጨምር ግን መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በህዋላ እና ከምግብ በፊት እጅን በመደበኛነት መታጠብ ያስፈልጋል።

ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ አየር ላይ የሚቆይነው?

እስካሁን የተደረጉ ጥናቶች ኮቪድ-19 ከአየር ወለድነት ይልቅ በዋነኝነት ከአፍ ወይም ከአፍንጫ ውስጥ ከሚወጡ እርጥብት አዘል ብናኞች ጋር በሚደረግ ግንኙነት እንደሚተላለፍ ይጠቁማሉ፤ ኮቪድ-19 እንዴት ነው የሚተላለፈው ለሚለው ጥያቄ የተሰጠውን መልስ ይመልከቱ

ኮቪድ-19 እንዴት ነው የሚሰራጨው?

 • 🤧 ሰዎች ፤ ቫይረሱ ካለባቸው ከሌሎች ሰዎች ፤ ኮቪድ-19 ሊይዛቸው ይችላል
 • 💦 በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ሲያስል፣ ሲያወራ ወይም ሲያስነጥስ ከአፍንጫ ወይም ከአፍ ውስጥ በሚወጡ እርጥብት አዘል ብናኞች አማካኝነት ከሰው ወደሰው ሊተላለፍ ይችላል
 • 🥄 እነዚህ እርጥብት አዘል ብናኞች  በእቃዎች ወይም ወለሎች ላይ ሊያርፉ ይችላሉ
 • 👈 ሰዎች እነዚህን እቃዎች ወይም ወለሎች ነክተው አይናቸውን አፍንጫቸውን ወይም አፋቸውን በመንካት በኮቪድ-19 ሊያዙ ይችላሉ
 • ↔️ ሰዎች በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በሚያስልበት፣ በሚያወራበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ የሚያስወጡትን እርጥብት አዘል ብናኞች በሚተነፍሱበት ጊዜ ወደ ውስጥ በማስገባት በበሽታው ሊያዙ ይችላሉ፤ ለዚህም ነው በበሽታው ከተያዘ ሰው 2 ሜትር(2 የአዋቂ እርምጃ) መራቅ አስፈላጊ የሆነው
 • የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19ን ስርጭት በተመለከተ ቀጣይ ጥናቶችን እያደረገ ነው፤ ወቅታዊ ግኝቶችንም ማጋራት ይቀጥላል

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሪፖርት እንዳደረጉ ከሚታወቁ አካባቢዎች የሚላኩ እቃዎችን መቀበል ለበሽታው አያጋልጥም?

አያጋልጥም፤ አንድ ሰው ለንግድ የሚላኩ እቃዎችን የመበከል እድሉ ትንሽ ነው፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በተላከ በተጓጓዝ እና ለተለያየ ሁኔታ እና የአየር ንብረት በተጋለጠ እቃ አማካኝነት ለኮቪድ-19 ለሚዳርገው ኮሮና ቫይረስ የመጋለጥ እድሉም አናሳ ነው

ከኢትዮጵያ ውጪ ወዳሉ ሃገራት ሄደው እየተመለሱ/ተመልሰው ከሆነ ምን ማድረግ አለቦት?

 • ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 እየተሰራጨ ወዳለበት አገራት ሄደው ከነበረ  መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች
 • የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ ያድርጉ:
 • ከውጪ ሃገር ለመጡ ሰዎች በተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ መቆየት
 • በቆይታዎ ወቅት ቫይረሱን ልመከላከል የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶች ይተግብሩ
 • በለይቶ ማቆያ የሚወጡ ህጎችን ያክብሩ
 • የበሽታው መልክቶች ከታዩቦት ለጤና ባለሙያዎች ወይም 8335 / 952 በመደወል ያሳውቁ
 • ከለይቶ ማቆያ ከወጡም በኋላ የመከላከያ ተግባራትን ይፈጽሙ
 • በተለያዩ አጋጣሚዎች ለይቶ ማቆያ ሳይገቡ ወደ ሃገር ከገቡ ወደ 8335 / 952 በመደወል ያሳውቁ

ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ አየር ላይ የሚቆይነው?

እስካሁን የተደረጉ ጥናቶች ኮቪድ-19 ከአየር ወለድነት ይልቅ በዋነኝነት ከአፍ ወይም ከአፍንጫ ውስጥ ከሚወጡ እርጥብት አዘል ብናኞች ጋር በሚደረግ ግንኙነት እንደሚተላለፍ ይጠቁማሉ፤ ኮቪድ-19 እንዴት ነው የሚተላለፈው ለሚለው ጥያቄ የተሰጠውን መልስ ይመልከቱ

የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች

የአፍ እና የአፍንችጫ መሸፈኛን እንዴት መጠቀም እንዳለብዎት፥ እንዴት እንደሚያወልቁ እና እንዴት እንደሚያስወግዱ ያውቃሉ?

 1. የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ያለባቸው ጤና ላይ የሚሰሩ ሰዎች፥ በሽተኞችን የሚንከባከቡ ሰዎች የመተንፈሻ አካላት ህመም ምልክቶች (እንደትኩሳት እና ሳል) እየተሰማቸው ያሉ ሰዎች እና ማንኛውም ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ያሉ ሰዎች ናቸው
 2. የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ከመንካትዎ በፊት እጅዎን ከአልኮል በተሰራ ማጽጃ ወይም በሳሙና እና በውሀ ያጽዱ
 3. የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ክፍተት እንዳለው ወይም ተቀዶ እንደሆነ ይመልከቱ
 4. ከላይ መሆን ያለበት የትኛው ጎን እንደሆነ ይመልከቱ (ብረቱ ያለበት ጎን)
 5. የውጭኛው ክፍል በውጪ በኩል መሆኑን ያረጋግጡ(የቀለመው ክፍል)
 6. የአፍ እና የአፍንችጫ መሸፈኛን ፊትዎ ላይ ያድርጉ፤ ትክክለኛውን ቅርጽ እንዲይዝ ብረቱን ወይም ጠንከር የሚለውን ክፍል በአፍንጫዎ ላይ ይጫኑት
 7. አፍንጫዎን፣ አፍዎን እና አገጭዎን እንዲሸፍን የአፍ እና የአፍንችጫ መሸፈኛን ወደታች ይጎትቱት
 8. ከተጠቀሙ በህዋላ የተበከለው የአፍ ጭምብል ልብስዎትን እና ፊትዎን እንዳይነካዎት ተጠንቅቀው ከጆሮዎት ጀርባ ያለውን ማሰሪያ ብቻ በመያዝ (በመፍታት) ያስወግዱት
 9. ተጠቅመው እንደጨረሱ የአፍ እና የአፍንችጫ መሸፈኛን ክዳን ባለው ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጣሉት
 10. የአፍ እና የአፍንችጫ መሸፈኛን ከነኩ ወይም ካስወገዱ በኋዋላ የእጅዎን ንጽህና ይጠብቁ – እጅዎን ከአልኮል በተሰራ ማጽጃ ያጽዱ ወይንም በሚታይ ሁኔታ ከቆሸሸ በውሀ እና በሳሙና ይታጠቡ።

ተጨማሪ ፥ አንዴ መሸፈኛውን ካደረጉ በኋላ አይነካኩት።

ማድረግ የሌለብኝ ነገር አለ?

የሚከተሉት እርምጃዎች በ COVID-19 ላይ ውጤታማ አይደሉም እና ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ

 • 🚭ማጨስ
 • 😷ከአንድ በላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን ደራርቦ መጠቀም
 • 💊አንቲባዮቲክሶችን መውሰድ

በማንኛውም አጋጣሚ ትኩሳት ሳል ወይም የመተንፈስ እክል ካጋጠምዎት ይበልጥ ከባድ ለሆነ በሽታ እንዳይጋለጡ በቶሎ በ8335 ወይም 952 ወይም በክልል ነጻ የስልክ መስመሮች ወይም በአካባቢዎ ያለ ጤና ተቋም በመሄድ የህክምና አገልግሎት ያግኙ፤ አገልግሎት ለሚሰጥዎት ሰው በቅርብ ጊዜ ጉዞ አድርገው ከነበረ ይናገሩ

ራስዎን ከበሽታው ይከላከሉ: የአፍንችጫ መሸፈኛን መቼ ነው ማድረግ ያለብን?

 • ይሄንን ቪዲዮ ይመልከቱ:

 • የአፍንችጫ መሸፈኛን መቼ ነው ማድረግ ያለብን*😷
 • ህዝብ የተሰበሰበባችው ቦታዎች ላይ ስንሄድ ማለትም እንደ ባንክ ፣ ታክሲ / አውቶቡስ ሰልፍ፣ ትራንስፖርት ውስጥ፣ ገበያ፣ ህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እና የመሳሰሉት
 • የታመመ ሰው እያስታመሙ ከሆነ
 • እያሳልዎ ወይም እያስነጠስዎ ከሆነ የአፍ የአፍንችጫ መሸፈኛን ይጠቀሙ
 • የአፍ ጭምብሎች ውጤታማ የሚሆኑ ጎን ለጎን እጃችንንም ከአልኮል በተሰራ ማጵጃ ወይንም በውሀ እና በሳሙና የምንታጠብ ከሆነ፣ አካላዊ ርቀታችንን ምንጠበቅ ከሆነ እንዲሁም ሌሎች ጥንቃቄዎች እምናደርግ ከሆነ ብቻ ነው
 • የአፍ የአፍንችጫ መሸፈኛን የሚጠቀሙ ከሆነ እንዴት እንደሚያደርጉት እና እንዴት እንደሚያወልቁትም ማወቅ አለብዎት

እራስዎን ይከላከሉ: ዋና ዋናዎቹ

 • እራስዎን እና ሌሎችን ከበሽታው ለመከላከል የሚከተለውን ቪድዮ ይመልከቱ:

 • እራስዎን ይከላከሉ
 • እጅዎን በተደጋጋሚ ይታጣቡ🧼
 • እጅዎን በመደበኛነት ከአልኮል በተሰሩ ማጽጃዎች ወይም በውሀ እና በሳሙና በደንብ ይታጠቡ
 • ለምን? እጅዎን በመደበኛነት ከአልኮል በተሰሩ ማጽጃዎች ወይም በውሀ እና በሳሙና መታጠብ እጅዎ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ ቫይረሶችን ስለሚገድል ነው
 • አካላዊ መራራቅን ይተግብሩ↔
 • ከማንኛውም ከሚያስል ወይም ከሚያስነጥስ ሰው 2 ሜትር(2 የአዋቂ እርምጃ) ያህል ይራቁ
 • ለምን? ሰዎች ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ ከአፍንጫቸው እና ከአፋቸው ቫይረሱን የያዘ ብናኝ ይረጫል፤ በጣም ከተጠጋጋችሁ የሚያስነጥሰው ወይም የሚያስለው ሰው በኮቪድ-19 የተያዘ ከሆነ ይሄንን ቫይረስ ወደ ውስጥዎ ሊያስገቡ ይችላሉ
 • የመተንፈሻ አካላትን ንጽህና ይጠብቁ 🤧
 • እርስዎና በአካባቢዎ ያሉ ሰዎች ጥሩ የሆነ የመተንፈሻ አካላትን ንጽህና እየጠበቁ እንደሆነ እርግጠኛ ይሁኑ፤ ይሄም ማለት በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉ ወቅት አፍን እና አፍንጫን በውስጥ ክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን ማለት ነው፤ ከዛም የተጠቀሙበትን ሶፍት ወዲያው ያስወግዱ
 • ለምን? ከመተንፈሻ አካላት የሚወጡ ፈሳሾች ቫይረስን ያሰራጫሉ የመተንፈሻ አካላትን ንጽህና መጠበቅ እራስዎ እና በአካባቢዎ ያሉ ሰዎች እራሳቸውን ከጉንፋን እና ከኮቪድ-19 እንዲከላከሉ ይረዳል
 • 🏠 ከቻሉ እቤትዎ ይቆዩ፤ ትኩሳት ሳል ወይም መተንፈስ ከከበዶት በ8335 / 952 ይደውሉ ወይም ወደ ጤና ተቋማት ይሂዱ፤ በአካባቢዎት ያለ የጤና ባለስልጣን የሚያወጧቸውን ህጎች ያክብሩ&nbsp;<br>_ለምን?_በአካባቢዎ ያሉ የጤና ባለስልጣናት ወቅታዊ የሆነ መረጃ ይኖራቸዋል፤ ደውለው በሚያሳውቁበት ጊዜ አገልግሎት ከሚሰጦት ሰው የት ሄደው ትክክለኛ ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ ይነግሮታል፤  ይሄ ደግሞ እራስዎትንም ሆነ በአካባቢዎት ያሉ ሰዎች ከበሽታው ስርጭት ለመከላከል ይጠቅማል፤
 • 🧳 ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ የተባባሱባቸውን ቦታዎች ይወቁ(ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያሉባቸውን ሀገሮች ወይም ከተማዎች) የሚቻል ከሆነ እነዚህ ቦታዎች ከመንቀሳቀስ ይቆጠቡ  – በተለይ ደግሞ እድሜዎት ከፍ ያለ ከሆነ የስኳር፣ የልብ፣ የሳንባ በሽታ ወይም ሌሎች ህመሞች ያለብዎት ከሆነ

እራሴን ከበሽታው ለመከላከል እና የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ምን ማድረግ እችላለሁ?

 • አንዳንድ ቀላል ጥንቃቄዎችን በመውሰድ በበሽታው የመያዝ አደጋን ወይም የበሽታውን ስርጭት መቀነስ ይችላሉ
 • 🧼 እጅዎን ከአልኮል በተሰሩ ማጽጃዎች ወይም በውሀ እና በሳሙና በመደበኛነት በሚገባ ያጽዱ
 • ለምን? በእጃችን ብዙ እቃዎችን ስለምንነካ እጃችን በቫይረሱ ሊበከል ይችላል፤ በተበከለ እጆችዎ ቫይረሱን ወደ ዓይኖችዎ ፣ ወደ አፍዎ ወይም ወደ አፍንጫዎ ያስተላልፉታል ፡፡ ከዚያ ቫይረሱ ከሰውነትዎ ውስጥ ገብቶ ሊያሳምሞት ይችላል
 • ከማንኛውም ሰው ቢያንስ 2 ሜትር (2 የአዋቂ እርምጃ) ርቀት ይኑርዎት
 • ለምን? አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ሲያስል እና ሲያስነጥስ በቅርብ ርቀት ውስጥ ካለን ከአፍና አፍንጫው የሚወጡትን ብናኞች ወደ ውስጣችን (በአፋችን፣ በአፍንጫችን ወይም በዓይናችን) ልናስገባ እንችላለን
 • 🚫 አይንዎን አፍንጫዎን እና አፎን ከመንካት ይቆጠቡ
 • ለምን? እጃችን ብዙ ነገሮችን ይነካሉ፣ እነዚህ ነገሮች ደግሞ በኮሮና ቫይረስ የተበከሉ ሊሆኑ ስለሚችሉ አይናችንን፣ አፍንጫችንን ወይም አፋችንን ከነካን ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ሊገባ ይችላል።
 • 🏠 በተቻለ መጠን እቤትዎ ይቆዩ፤ ትኩሳት ሳል ወይም መተንፈስ ከከበዶት በ8335 / 952 ይደውሉ ወይም ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ፤ በአካባቢዎት ያለ የጤና ባለስልጣን የሚያወጡትን ህግ ያክብሩ
 • ለምን? በአካባቢዎ ያሉ የጤና ባለስልጣናት ወቅታዊ የሆነ መረጃ ይኖራቸዋል፤ ደውለው በሚያሳውቁበት ጊዜ አገልግሎት ከሚሰጦት ሰው የት ሄደው ትክክለኛ ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ ይነግሮታል፤ ይሄ ደግሞ እራስዎትንም ሆነ በአካባቢዎት ያሉ ሰዎች ከበሽታው ስርጭት ለመከላከል ይጠቅማል፤
 • 🧳 ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ የተባባሱባቸውን ቦታዎች ይወቁ(ኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያሉባቸውን ሀገሮች ወይም ከተማዎች) የሚቻል ከሆነ ኮቦታ ቦታ ከመንቀሳቀስ ይቆጠቡ – በተለይ ደግሞ እድሜዎት ከፍ ያለ ከሆነ እና የስኳር የልብ ወይም የሳንባ በሽታ ያለብዎት ከሆነ
 • ለምን? እነዚህ ቦታዎች በኮቪድ-19 የመያዝ አደጋን ከፍተኛ ስለሚያደርጉ

ሌሎች

በኮቪድ-19 የመያዝ ተጋላጭነቴ  ምን ያህል ነው?

 • የእያንዳንዱ ሰው ተጋላጭነት እንዳሉበት ቦታ ይለያያል- በተለይ ደግሞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባሉባቸው ቦታዎች (አገሮች)
 • የተለያዩ ቦታ ለሚኖሩ ብዙ ሰዎች በኮቪድ-19 የመያዝ እድል ከፍተኛ ነው፤ አዳዲስ በበሽታው የሚያዙ ቁጥሮች በተገኘ ቁጥር መንግስታት እና የጤና ባለሙያዎች የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው፤ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስን አስመልክቶ የሚወጡትን ህጎች ማክበርዎትን እርግጠኛ ይሁኑ፤ በሽታውን ለመቆጣጠር ለሚደረጉ ጥረቶች መተባበር በኮቪድ-19 የመያዝን እድል እና የበሽታውን ስርጭት ይቀንሰዋል
 • የኮቪድ-19ን ወረርሽኝ መቆጣጠር እና ስርጭቱን ማስቆም ይቻላል፤ ይሄ በቻይና እና በአንዳንድ ሀገራት እየታየ ነው፤
 • “ውቅታዊ የበሽታውን መረጃ ለማግኝት ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ ከስር ባለው የመረጃ መረብ  ገብተው ይመልከቱ https://www.who.int/emergencies/diseases/novel-coronavirus-2019/situation-reports/

የተሳሳተ መረጃ  እንደሆነ በምን አውቃለሁ?

 • የዓለም ጤና ድርጅት ነን ከሚሉ ወንጀለኞች ተጠንቅቁ
 • የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 አደጋን  ተጠቅመው ሀሰተኛ መልእክቶችን የሚልኩ እንዳሉ ይታወቃል

እነዚህ ሀሰተኛ ኢሜሎች የዓለም ጤና ድርጅት ነን ብለው እነዚህን ጥያቄዎች ያቀርብልዎታል፡

 • አድራሻዎትን እና ማለፊያ ቃልዎን ይጠይቃሉ
 • የሚያጋልጡ ሊንኮችን እንዲነኩ ይጠይቆታል
 • የሚያጋልጡ መረጃዎችን እንዲከፍቱ ያደርጎታል

ይሄንን መንገድ ተጠቅመው መረጃዎችን ይወስዳሉ

ከሀሰተኞች እንዴት መራቅ ይችላሉ?

 • ✅ ኢሜላቸውን በማየት ማወቅ ይችላሉ፤ የዓለም የጤና ድርጅት ኢሜል መጨረሻው እንደዚህ ነው፡ *@who.int*
 • 🔗 ከመክፈትዎ በፊት ሊንኩን ያጣሩ: እውነተኛ ሊንኮች የሚጀምሩት እንደዚህ ነው https://www.who.int.
 • 🤐 የግል መረጃዎትን ሲሰጡ ይጠንቀቁ: መረጃዎችን ለማግኘት የእርስዎ ስምና የይለፍ ቃል የሚያስፈልግበት ምክንያት የለም
 • ⏲️ አይቸኩሉ: እንደዚህ አይነት መረጃዎች ውሳኔዎችን በፍጥነት እንዲያደርጉ ያስገድድዎታል፤ ጥያቄው ትክክለኛ እንደሆነ ያጣሩ
 • 📄 ወሳኝ መረጃን ሰጥተው ከሆነ አይጨነቁ ወዲያውኑ መረጃዎትን ይቀይሩ
 • ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት ይሄንን ይጫኑ: https://www.who.int/about/communications/cyber-security

የስራ ቦታ

 • ይሄንን ቪድዮ ይመልከቱ(33 ደቂቃ):

 • የዓለም ጤና ድርጅት እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የህዝብ ጤና ባለስልጣናት ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው፤ ሆኖም ዘላቂ መፍትሄ በቀላሉ አይገኝም፤ ወረርሽኙን ለማቆም ሁሉም የህብረሰባችን አካል ነጋዴዎችም ሆኑ ቀጣሪዎች የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው
 • ቀጣሪዎች ምን ማድረግ መጀመር እንዳለባቸው ማወቅ ከፈለጉ ይሄንን መረጃ ጭነው ማንበብ ይችላሉ፤ በሚሰሩበት አካባቢ ኮቪድ-19 ባይከሰትም እንኳን

ስለኮቪድ-19 መስጋት አለብኝ?

 • ይህ በሽታ ከ100 ሰው 20 ሰው ላይ ከባድ ህመም ያስከትላል፡ በተጨማሪም በዚህ በሽታ ለሞት የሚዳረጉ ሰዎች አሉ፡ በተለይ ይህ በሽታ እድሜያቸው የገፋ፣ ረጅም ጊዜ የጤና ክትትል የሚፈልጉ እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ከባድ ህመም እና ሞትን የማስከትል እድሉ ከፍተኛ ነው።
 • ይሄንን ስጋታችንን እራሳችንን የምንወዳቸውን እና ህዝባችንን ለመጠበቅ ልንጠቀምበት እንችላለን፤ የመጀመርያው እና ዋነኛው እጃችንን በደንብ መታጠብ እና ስናስል እና ስናስነጥስ አፍና፣ አፍንጫችንን በሶፍት ወይም ክንዳችችንን በማጠፍ መሸፈን፤ ሁለተኛ አካላዊ ርቀታችንን ከማንኛውም ሰው በ2 የአዋቂ እርምጃ መጠበቅና ሌሎችም ናቸው።
 • እራስዎን እንዴት መከላከል እንዳለብዎት ለማወቅ ይሄንን ይመልከቱ https://www.who.int/emergencies/diseases/novel-coronavirus-2019/advice-for-public

ሀሰተኛ መረጃዎች

 • ሀሰተኛ መረጃ፡ አዲሱ ኮሮና ቫይረስ የሚያጠቃው በእድሜ የገፉ ሰዎችን ብቻ ነው ወይስ ወጣቶችም በበሽታው ሊያዙ ይችላሉ?
 • በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ ይችላሉ፤ በእድሜ የገፉ ሰዎች እና አስቀድሞ እንደአስም፥ ስኳር እና የልብ በሽታ አይነት በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች በዚህ ቫይረስ በጠና የመታመም አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላሉ
 • የጤና ሚኒስቴር በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች እራሳቸውን ከበሽታው ለመከላከል እርምጃ እንዲወስዱ ይጠይቃል

ሀሰተኛ መረጃ: አዲሱን ኮሮና ቫይረስ  በአንቲባዮቲክስ መከላከል ወይም ማከም ይቻላል?

 • አንቲባዮቲክስ ቫይረስን አያጠፉም፤ አንቲባዮቲክስ የሚሰራው ለባክቴሪያ ነው
 • አዲሱን ኮሮና ቫይረስ ለመከላከልም ሆነ በሽታውን ለማከም አንቲባዮቲክስ መጠቀም አያስፈልግም
 • ሆኖም በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል ከተኙ፤ የባክቴሪያ ኢንፌክሽንም ሊይዞት ስለሚችል አንቲባዮቲክስ ሊሰጥዎት ይችላል

ሀሰተኛ መረጃ:  በሙቅ ውሀ መታጠብ ቫይረሱን ይከላከለዋል?

በሙቅ ውሀ መታጠብ በኮቪድ-19 ከመያዝ አይከላከልም፤ በሙቅ ውሀ ቢታጠቡም ትክክለኛ የሰውነት ሙቀትዎ በ36.5 እና በ37 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መሀል ነው የሚሆነው፤ እንደውም በጣም ትኩስ በሆነ ውሀ ገላን መታጠብ ሊያቃጥሎት ስለሚችል አደገኛ ነው፤ ከኮቪድ-19 እራስዎን ለመከላከል ትክክለኛው አማራጭ እጅዎን በተደጋጋሚ መታጠብ ነው፤ ይሄንን በማድረግ እጅዎ ላይ ያሉ ቫይረሶችን ያስወግዳሉ፤ በእጅዎ አይንዎን አፍዎን ወይም አፍንጫዎን በመንካት በቫይረሱ የመያዝ አደጋም አይኖርቦትም በተጨማሪም አካላዊ ርቀትን መጠበቅዎን እና ሌሎችንም የመከላከያ መንገዶች ይተግብሩ።

ሀሰተኛ መረጃ፡ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ቫይረሱን ይገድለዋል?

ቀዝቃዛ አየር ኮሮና ቫይረስንም ሆነ ሌሎች ቫይረሶችን እንደሚገድል የሚያሳምን ምንም ምክንያት የለም፤ የውጭኛው አየር ምንም አይነት ቢሆን የሰው የሰውነት ሙቀት በ36.5 እና በ37 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መሀል ነው ከኮቪድ-19 እራስዎን ለመከላከል ትክክለኛው አማራጭ እጅዎን በተደጋጋሚ ከአልኮል በተሰራ ማጵጃ ወይንም በውሀ እና በሳሙና መታጠብ ነው&nbsp;በተጨማሪም አካላዊ ርቀትን መጠበቅዎን እና ሌሎችንም የመከላከያ መንገዶች ይተግብሩ።

ጠቃሚ ድህረ-ገጾች

Join over 6,000 subscribers for Jegna stories and new opportunities.

We use cookies to give you the best experience.